ለኢንስቲትዩቱ አመራርና ሰራተኞች የመልካም አስተዳደር ስልጠና ተሰጠ፤

ለአማራ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አመራርና ሰራተኞች በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ታህሳስ 21/2013 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በመድረኩ መክፈቻ ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ እንደዚህ ዓይነት ስልጠናዎችን በተከታታይ መሰጠት እንዳለበት ገልፀው የኢንስቲትዩቱን ራዕይ በማሳካት በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ተወዳዳሪ ተቋም ለመፍጠር በጋራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ስልጠናውን የሰጡት የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ መምህር አቶ የሻምበል አጉማስ ሲሆኑ በተቋሙ ያሉ ችግሮችን ለይቶ ማስወገድ፣ ጥናትና ምርምር ማካሄድ እንዲሁም ሳይንስን፣ ፍልስፍናንና ጥበብን አዋህዶ በመስራት ህብረተሰባችሁን በቅንነት ማልገል እንዳባቸው አስረድተዋል፡፡ አቶ የሻምበል አያይዘውም የተቋሙ አመራሮች ከሰራተኞች ጋር የሚገናኙበት ቋሚ የሆነ መድረክ በማመቻት የስራ ፍልስፍቸውን ማሳወቅ እንዲሁም ሁሉም አመራርና ሰራተኛ የተመደበበትን የስራ ሃላፊነት በመወጣት ለተቋሙ ለውጥ በጋራ በመስራት እንዳባቸው አሳስበዋል፡፡ የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በስልጠናው እውቀት ያገኙበት እና ለስራቸው አጋዥ መሆኑን ገልፀው ወደፊት እንደዚህ ዓይነት ስልጠናዎች ቢሰጡ መልካም ነው ብለዋል፡፡
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *