ሙያዊ ስነ-ምግባርን የተላበሰ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፤

ለአማራ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አመራርና ሰራተኞች ለስራ ምቹ የሆነ የአሰራር ስልትና ባህል በተቋሙ ለማዳበር የሚያግዝ ስልጠና ጥር 8/2013 ዓ.ም ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናዉ የተቋሙን ግቦች ከማሳካት አኳያ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች መልካም ስነ-ምግባርን በተላበሰ መልኩ አገልግሎት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ሲሆን በስልጠናዉ በስነ-ምግባር ዙሪያ ያላቸውን ክህሎት በማጎልበትና በቂ ግንዛቤ በመያዝ የተጣለባቸዉን ኃላፊነት በቅንነትና በታማኝነት ለመወጣት ሙያዊ ስነ-ምግባርን የተላበሰ የህዝብ አገልጋይነት መንፈስን ለማጎልበት ጥቅም ያለዉ ነዉ፡፡ ስልጠናዉ የተሰጠዉ በአቶ ሞላ በላይ እና አቶ ዘላለም ንጉሴ ሲሆን ርኅራኄ፣ አክብሮትና እንክብካቤ እና ሙያዊ ስነ-ምግባርን የተላበሰ አገልግሎት አሰጣጥ፣ የደንበኞች አያያዝና የተግባቦት ክህሎት፣ በሚሉ ርዕሶች ሲሆን በማንኛዉም ሁኔታ ማንነትንና የግለሰቦችን ክብር በማይነካ መንገድ በጥሩ ስነ-ምግባር አገልግሎት መስጠት እንደሚገባም ግንዛቤ ተፈጥሯል፡ በአገልግሎት አሰጣጥና ቅሬታ ማስተናገጃ የስራ ክፍል የተከናወኑ ተግባራት በስራ ክፍሉ ባለሙያ ወይዘሮ የሽወርቅ ፈቃዴ የቀረበ ሲሆን የቅሬታ ምንጭ የሆኑ አሰራሮችና አፈፃፀሞችን ለመለየት የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት መከናወኑ፣ አገልግሎት ሰጭና ተቀባይ መብትና ግዴታዎችን እንዲያዉቁ ማድረግ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሚከሰቱ አለመግባባቶችን እንዲፈቱ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎችም አቅርበዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች በተሰማራንበት የስራ መስክ ጠንክረን እንድንሰራ የሚያነቃቁና የህዝብ አገልጋይነታችንን የሚያጎለብት ስለሆኑ ተጠናክረዉ መቀጠል አለባቸዉ ብለዋል፡፡ አሕጤኢ 10/5/2013 ዓ.ም
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *