በአማራ ክልል ሁለተኛውን የልጅነት ልምሻ (የፖሊዮ) በሽታ ለመከላከያ የክትባት ዘመቻ እየተካሄደ ነው

ፓሊዮ ቫይረስ ሕፃናትን ለህመም፣ ለሞት እና ለዘላቂ አካል ጉዳተኛነት የሚዳርግ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ አምጪ ተህዋስ ነው፡፡ በሽታውን መከላከል የሚቻለው ህፃናትን በመደበኛ የክትባት መርሃ ግብር እና በዘመቻ መልክ የሚሰጠውን የማጠናከሪያ ክትባት በአግባቡ እንዲከተቡ በማድርግ ነው፡፡ የልጅነት ልምሻ (የፖሊዮ) በሽታ በአማራ ክልል በነሐሴ ወር 2012 ዓ.ም ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በመከሰቱ ምክንያት በተሰራው የተጋላጭነት ዳሰሳ መሰረት በአማራ ክልል በተመረጡ 3 ዞኖች /ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር/ እንዲሁም ደሴ ከተማ አስተዳድር በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና ቀበሌዎች ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የመጀመሪያ ዙር ክትባት ከህዳር 18-21 ቀን 2013 ዓ/ም እንደተሰጠ ይታወቃል፡፡ ሁለተኛው ዙር የልጅነት ልምሻ (የፖሊዮ) በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከታህሳስ 9-12 ቀን 2013 ዓ.ም እየተካሄደ ሲሆን በእነዚህ ቀናት ክትባቱን የሚሰጡ ባለሙያዎች ወደየቤታችሁ ስለሚመጡ እድሜአቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ከዚህ በፊት የፖሊዮን ክትባት ቢከተቡም ባይከተቡም ሁለተኛውን ዙር ክትባት መውሰድ አለባቸው፡፡ ወላጆችና አሳዳጊዎች በተጠቀሰው ቀናት ልጆቻችሁን እንድታስከትቡ እያሳወቅን በሚያስከትቡበት ጊዜ የኮኖና በሽታ መከላከያ የጥንቃቄ መንገዶችን ማለትም እጅን በተደጋጋሚ በመታጠብ፣ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅና አፍና አፍንጫን በመሸፈን እንዲሁም ቤት በመቆየት ራስዎንና ቤተሰብዎን ከኮሮና ቫይረስ ይጠብቁ፡፡
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *