በአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የልምድ ልውውጥ ተካሄደ፤

ከደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮና ከተለያዩ ተቋማት የተዉጣጡ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በክልሉ የህብረተሰብ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ለማቋቋም በአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የልምድ ልዉዉጥ አካሄዱ፡፡ የክልሉን ላቦራቶሪ ማዕከል ወደ ህብረተሰብ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ደረጃ ለማሸጋገርና ተሞክሮ ለመቀመር ባለሙያዎችና የስራ ሃላፊዎች በአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመገኘት አጠቃላይ በኢንስቲትዩቱ መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ የተከናወኑ ተግባራት፣ ጠንካራና ያጋጠሙ ችግሮች በተቋሙ የስራ ሃላፊዎችና ዳይሬክቶሬቶች ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ጎብኝዎችም በየዳይሬክቶሬቶች በመዘዋወር የስራ እንቅስቃሴዎችንም ጎብኝተዋል፡፡ አስተያየታቸዉን ከሰጡን መካከል አቶ ማሙሽ ሁሴን፣ አቶ ሙሃመድ አይኔ እና ወ/ሮ እመቤት መኮነን ለክልል ብቻ ሳይሆን ለሃገር የሚጠቅም ስራ እየተሰራ መሆኑን፣ የተቀላጠፈና የተቀናጀ የአሰራር ስርዓት የተዘረጋ መሆኑን፣ የተደራጀ የአደጋ ጊዜ ማሳለጫ ማዕከል ማቋቋም መቻሉ፣ ክልሉ ላይ የሚሰሩ ጥናቶች ወደ አንድ ቋት እየገቡና የገቢ ምንጭ እየሆኑ መሆናቸዉ በአጠቃላይ በልምድ ልዉዉጡ በቂ መረጃ እንዳገኙበትና ለሚፈልጉት ዓላማ ግብዓት ማግኘታቸዉን ገልጸዋል፡፡ አህጤኢ 09/04/2012 ዓ.ም
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *