በአንድ አካባቢ የሚከሰት የሕብረተሰብ የጤና ችግር ለየትኛዉም ቦታ ስጋት በመሆኑ ተገለፀ፤

የስምምነቱ ዓላማ ሁለቱ ተቋማት የተለያዩ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ ጥናትና ምርምር ለመስራት፣ ስንቅ የሚል ወርሃዊ የዉይይት ፕሮግራም በማዘጋጀት ያለቁ የምርምር ስራዎች የፕሮግራም ሰዎች እንዲጠቀሙባቸዉና ጥቅም ላይ እንዲዉሉ ለማድረግ እንዲሁም በአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በጋራ ተባብረዉ ለመስራት ነው። ኢንስቲትዩት በህግ ከተሰጡት ተግባራት መካከል በህብረተሰብ ጤና ምርምር አጀንዳዎች ላይ ተመስርቶ ቅድሚያ ትኩረት በተሰጣቸዉ የጤና ችግሮች ላይ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ማካሄድ፣ ሳይንሳዊና ቴክኖሎጅያዊ እዉቀትን በማመንጨት፣ በመቅሰምና በማሰራጨት የህብረተሰቡን ጤና ማሻሻል ሲሆን ለዚህ ተግባር መሳለጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት ሚናዉ የጎላ በመሆኑ የስምምነት ሰነዱ ተፈርሟል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ በስምምነት ፊርማዉ ላይ እንደተናገሩት ዋናዉ የተቋሙ ምሰሶ የጤና ምርምር ላይ በትብብር በመስራት፣ የአቅም ግንባታ ስራ በመስራት እና ወደፊት ተመራማሪዎችን ማፍራት፣ ህብረተሰቡ ላይ ለዉጥ የሚያመጣ ችግር ፈች የሆነ ምርምር ማካሄድ ነው። በክልሉ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎችን ማስተባበርና የተሰሩትን ጥናቶች ሳይንሳዊ እንዲሆኑ ማድረግ ሲሆን ይህ በጋራ የመስራት የትብብር ፕሮግራም በክልላችን ላሉ ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሌሎችም በትብብር ለመስራት ፍላጎት ላላቸዉ ተቋማትና አጋር ድርጅቶች ትልቅ በር የሚከፍት ነዉ ብለዋል ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡ ልንተጋገዝባቸዉና አብረን ልንሰራባቸዉ የሚገቡ በርካታ ስራዎች አሉ ያሉት የፍኖተ ሃርቫርድ ፕሮጀክት ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ፅኑኤል ግርማ በሃገራችን በርካታ ያልተጠቀምንባቸዉ መረጃ፣ እዉቀትና የሰዉ ሀይል ያለ መሆኑን ገልፀው ኢንስቲትዩቱ ካለዉ እቅድና ዓላማ አኳያ ያለዉን የሰዉ ሃይል በማስተማርና ልምድ በማጋራት የሚሰሩ ችግር ፈች ምርምሮች ላይ ቴክኒካል ድጋፍ በማድረግ አብረዉ ለመስራት ፈቃደኛ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡ የፕሮጀክቱ ምክትል ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ምርኩዜ ወልዴ እና የፕሮጀክቱ አማካሪ ዶክተር ትዝታ ጥላሁን ካሁን በፊት ፕሮጀክቱ በሰራባቸዉ ክልሎች ያለዉን ልምድ ለኢንስቲትዩቱ አጋርተዋል፡፡ በመግባቢያ ስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓት ማጠቃለያ ላይ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማህተመ ኃይሌ ካሁን በፊት ሊያንቀሳቅሰን የሚችል አጋር አለመኖሩን ጠቅሰዉ ከዚህ በኋላ በተደራጀ መንገድ ተጠናክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡ አህጤኢ 7/5/2013 ዓ.ም
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *