በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና የጤና መድህን ተደራሽነት ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክና ዘመቻ ሊካሄድ ነዉ፤

“የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና የጤና መድህን ተደራሽነትን ማረጋገጥ የሁላችን ሃላፊነት ነዉ” በሚል ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ ሊካሄድ መሆኑን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታዉቀዋል፡፡ እንደ ዶክተር መልካሙ ገለፃ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በባለፈዉ ዓመት ጀምሮ በሃገራችን ብሎም በክልላችን በመከሰቱ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የማስተማር፣ የመለየት፣ የማከምና የመመርመር ስራዎች በስፋት መከናወናቸዉንና በንቅናቄ ሲሰራ የቆየ መሆኑን አዉስተዉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የመከላከያ መንገዶች አተገባበር በህብረተሰቡ ዉስጥ መቀዛቀዝ በመፈጠሩ ምክንያት የወረርሽኙ ስርጭት እየጨመረ በመሄዱ የንቅናቄ ዘመቻ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነዉ ብለዋል፡፡ የኮሮና ወረርሽኝን የመከላከል ስራ የሁሉም ሃላፊነት በመሆኑ ማንኛዉም ሰዉ የትኛዉንም አይነት አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት የመከላከያ መንገዶችን መተግበር እንደሚገባና በማህበረሰቡ ዉስጥ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በትኩረት መሰራት እንዳለበትም ገልፀዋል፡፡ ዶክተር መልካሙ አያይዘዉም ከኮቪድ-19 ትግበራ ጎን ሁሉንም ሰዉ ከድንገተኛ ወጭ የሚታደገዉን የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት በማጠናከር አዳዲስ አባላትን የማፍራትና የነባር አባላትን የማስቀጠል ስራ በንቅናቄዉ በትኩረት ይሰራል ተብሏል፡፡
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *