በወባ በሽታ መከላከል ላይ ማህበራዊ እና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጠ፤

በአማራ ክልል በ2013 በጀት ዓመት የፀረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭት በማይካሄድባቸዉ ወረዳዎች ለተዉጣጡ ከ80 በላይ የዞንና ወረዳ የህብረተሰብ ጤና አዳጋዎች መከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም ለወባ ባለሙያዎች መስከረም 12/2013 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ ስልጠና ተሰጠ፡፡ ስልጠናዉ በበጀት ዓመቱ የኬሚካል ርጭት በማይካሄድባቸዉ ቦታዎች በአካባቢ ቁጥጥር ስራ የማህበረሰቡን ተሳታፊነት ለማሳደግና በመኝታ አጎበር አጠቃቀም ላይ ያለዉን የአመለካከት ችግር ማህበራዊ እና የባህሪ ለውጥ ግንኙነትን ተግባቦትን በመጠቀም ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችል በወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር የተግባቦት ስራ ለመስራትና በአካባቢ ቁጥጥር ስራና የአጎበር አጠቃቀም ጋር በተገናኘ የሚስተዋሉ የተሳሳቱ አመለካከቶች በመኖራቸዉና ይህንንም ለመቅረፍ የሚሰሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ አፅንኦት ለመስጠት ነዉ፡፡ ማህበራዊ እና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት ለግለሰቦች የሚስማሙ አዎንታዊ ባህሪያትን ለማራመድ የግንኙነት ስትራቴጂዎችን ለማዳበር ከግለሰቦች፣ ከቡድን ወይም ከማህበረሰብ ጋር የሚደረግ ሲሆን ስትራቴጂክ ኮሙዩኒኬሽን የረጅም ጊዜ ራዕይን የሚያስተናግድ እንዲሁም በባህሪው እና በማህበራዊ ለውጥ መንስኤዎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ባለድርሻ አካላት እና ተጠቃሚዎች ንቁ ተሳትፎ የሚያከናውን ሂደት ነው ይህም ሰዎች በወባ ቁጥጥር ስራዎች አዎንታዊ እና ተፈላጊ ባህሪን እንዲጀምሩ፣ እንዲቀጥሉ እና እንዲጠብቁ ያስችላቸዋል፡፡ ከስልጠናዉ በኋላ ሰልጣኞች ወደ መጡበት ሲመለሱ ከማህበረሰቡ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸዉን ጤና ኤክስቴንሽኖችንና ባለሙያዎችን እንዲያሰለጥኑና ህብረተሰቡ አጎበርን ሁልጊዜና በአግባቡ እንዲጠቀም፣ የአካባቢ ቁጥጥር ስራ/ የወባ ትንኝ መራቢያ ቦታዎችን በማዳፈንና በማፋሰስ፣ የህመም ስሜት ሲኖር በወቅቱ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ህክምና በማግኘት የወባ በሽታን እንዲከላከሉ ለማድረግ ነዉ፡፡ አህጤኢ 13/1/13 ዓ.ም
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *