በጤናዉ ዘርፍ የሚሰሩ ጥናትና ምርምሮች የሚቀርቡበት ስንቅ “SINQ Session” በሚል ተቋቁሞ ዉይይት ተካሄደ፤

በአብክመ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከፍኖተ ሃርቫርድ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በጤናዉ ዘርፍ የሚሰሩ ጥናትና ምርምሮች የሚቀርቡበት ስንቅ “SINQ Session” በሚል ስያሜ የተቋቋመ ሲሆን በባህር ዳር ከተማ የካቲት 17/2013 ዓ.ም የመጀመሪውን ውይይት አካሄዷል፡፡ በመድረኩ የኢንስቲትዩቱ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታዬ ዘሩ የስንቅ “SINQ Session” ምንነት እና ዓላማው ላይ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን ፕሮግራሙ በየወሩ እንደሚካሄድ እና ከየትኛውም የአገሪቱ ክፍል የሚመጡ ተመራማሪዎች ጥናታቸውን ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የ“JSIL10K” ባለሙያ የሆኑት አቶ ግዛቸው ታደለ በጨቅላ ህጻናት ሞት “unacceptably high neonatal mortality in neonatal intensive care unit in hospitals of Ethiopia:systematic review and meta-analysis:: በሚል የተሰራ ጥናት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የዚህን ዓይነት ፕሮግራም በጤና ሚኒስቴር እና በኦሮሚያ ክልል በሰፊው እየተሰራበት እና ውጤት ያገኙበት መሆኑን የገለፁት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማህተመ ሃይሌ በመድረኩ ተወያይቶ መለያየት ብቻ ሳይሆን ለውጥ ለማምጣት መስራት ይጠበቃል ብለዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ መድረኩ የፕሮግራምና ፖሊሲ ባለሙያዎች ከተመራማሪዎች ጋር ተገናኝተው በችግሮች ላይ ተወያይተው መፍትሄ የሚያመጡበት ነው ካሉ በኋላ በአሁኑ ወቅት በምርምር የተረጋገጠ ማስራጃዎችን በማምጣት የህብረተሰባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በጋራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበለዋል፡፡ አሕጤኢ 18/06/2013 ዓ.ም
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *