Previous Next በአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የተቋቋመው ክልላዊ የዕዉቀት ቋት/Regional knowledge hub/ በጥናትና ምርምር ላይ ያተኮረ የዉይይት መድረክና ስልጠና ከታህሳስ 16-20/2012 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ አካሄደ፡፡ በመድረኩ ዓላማበጥናትና ምርምር ላይ ያተኮረ ስልጠና፣ የተጀመሩ 5 የምርምር ስራዎችን ያሉበትን ደረጃ ለመገምገም፣ systematic review and meta-analysis ስልጠና ለመስጠትና አስተያየቶችን ለመጋራት ነው፡፡ ስልጠናዉ የሚሰሩ ጥናቶችን ለማዳበርና ምርምሮች መረጃቸዉ በተሻለ ለማደራጀት የሚረዳ ሲሆን በየሩብ ዓመቱ የሚካሄድና ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከግል ጤና ተቋማትና ከአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚሳተፉበት ነዉ፡፡