አዲሱ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ከኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ጋር ትዉዉቅ አደረጉ፤

የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አዲስ የተመደቡት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ከኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ጋር የትዉዉቅ እንዲሁም በተከናወኑና ወደፊት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ያተኮረ የዉይይትና የምክክር መድረክ ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ ተካሄደ፡፡ በትዉዉቅ ስነ ስርዓቱና የተግባራት ዉይይት ወቅት ኢንስቲትዩቱ የተቋቋመባቸዉ ዋናዋና ዓላማዎች፣ ከተቋቋመበት ዓላማ አኳያ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት፣ የነበሩ ክፍተቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ወደፊት መከናወን ያለባቸዉ ተግባራት በዝርዝር ለዉይይት መነሻ የሚሆን ፅሁፍ በእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተሰጋ መንግስቱ አቅርበዋል፡፡ ከኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ጋር በይፋ ትዉዉቅ ያደረጉት አዲሱ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ተቋሙ እያከናወናቸዉ ካሉ ስራዎች ጎን ለጎን ተጨማሪና ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ትኩረት በሚያስፈልጋቸዉ ተግባራት ዙሪያ መነሻ ሃሳቦችን ያቀረቡ ሲሆን የኢንስቲትዩቱን ገፅታ ከፍ ለማድረግ ከአመራሮችና ሰራተኞች ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸዉን ገልፀዉ የሁሉም ትብብር በጣም ያስፈልጋልና በጋራ እንሰራለን የሚል መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡ በዉይይቱም በዳይሬክተሩ ሊከናወኑ የታሰቡና መነሻ ሃሳቦች የሚበረታቱና ተቋሙን ወደ ተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ መሆናቸዉንና ሁሉም የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሰራተኛ አንድ በመሆን ግንባር ቀደም ተቋም ለማድረግ በርብርብ መስራት እንደሚያስፈልግም ተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡ በመድረኩ የኢንስቲትዩቱ የደሴና ባህርዳር አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ከጤና ቢሮ ተሳትፈዉበታል፡፡
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *