-ኢንስቲትዩቱ ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የምክክር መድረክ አካሄደ፤

የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር በክልሉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን እና የመንገድ ትራንስፖርት ደህንነት ማረጋገጥና አደጋ የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባር ላይ የምክክር መድረክ አካሄደ፤ በመድረኩ የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከልና ትራፊክ ምክትል ዘርፍ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሙሉ ሁነኛው በመክፈቻ ንግግር ላይ እንደገለፁት በክልሉ በርካታ ሃይል በማሳተፍ በትራፊክ አደጋ፣ ወንጀል መከላከል እንዲሁም የኮሮና ወረርሽን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በጋራም ሆነ በተናጠል በርካታ ውጤታማ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በቀጣይም ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመቀናጀት የተሻለ ስራ መስራት አለብን ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መህተመ ሃይሌ በበኩላቸው የፖሊስ ሃይሉ የኮሮና ቫይረስ በክልላችን ከተከሰተ ጀምሮ ብርዱ፣ ፀሃዩና ጨለማው ሳይበግረው ከጎናችን በመሆን በርካታ ስራዎችን ሲሰራ የቆየ በመሆኑ አመስግነው በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ብሎም በክልላችን ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ስለሆነ ይህንን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም ቀጣይ በሚካሄደው አገር አቀፍ የምርመራ ስራ ላይ በጋራ መስራት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል፡፡ ኢንስቲትዩት የተቋቋመበትን ዓላማ፣ የሰራቸው ስራዎችን እና ወደፊት የሚከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ በኢንስቲትዩቱ የእቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ተሰጋ መንግስቱ ቀርቧል፡፡ የትራፊክ አደጋና እና የህብረተሰብ ጤና ተያያዥነትና የማይለያዩ መሆናውን የገለፁት የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዋና ክፍል ሃላፊ ዋና ኢ/ር ፅጌ አሻግሬ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማስፈፀም፣ ትምህርት መስጠት፣ እርምጃ መውሰድ እና የትራፊክ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር እና ሌሎች የተከናወኑ ተግባራትን አቅርበዋል፡፡ በመድረኩ ከሁሉም ዞኖች የፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዋና ክፍል ሃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን እና የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የታዩ ከፍተቶችን በመቅረፍ ወደፊት በቅንጅት እንዴት በመስራት እንዳለባቸው እና ሌሎች ሃሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ አህጤኢ/ ፍቅረማሪያም
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *