ኢንስቲትዩቱ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የምስጋና ሽልማት አበረከተ፤

በክልላችን የተከሰተውን የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስትዩት የምስጋና የምስክር ወረቀት ሽልማት አበረከተ፤
በምስጋና ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህራዊ ክላስተር አስተባባሪና የኮሮና ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ግብረ ሃይል ሰብሳቢ ዶክተር ሙሉነሽ አበበ እንዳሉት ወረርሽኙን ለመከላከል ራሳችሁንና ቤተሰባችሁን መስዋዕት አድርጋችሁ ለሰራችሁት ስራ መመስገን የሚገባቸው መሆኑን ገልፀው የተቋሙ ሰራተኞችም ይህንን ፕሮግራንም የመንግስት በጀት ሳይጠብቁ በራሳቸው ወጪ መዘጋጀቱን አድንቀዋል፡፡ የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ በበኩላቸው ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት የተቋሙ ሰራተኞች በሙሉ በመከላከልና በመቆጣጠር ሂደት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዉ ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡
የምስጋና የምስክር ወረቀት
1. የምርምና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት
2. የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
3. የህክምና መሳሪያዎች ጥገናና ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት
4. የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገም ዳይሬክቶሬት
5. የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት
የላቀ አስተዋፅኦ ያበረከቱ
1. የላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት
2. የግዥ፣ ፋይናንስና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት
3. የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት
4. የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ
ልዩ ተሸላሚ
1. የአማራ የመንገድ ህንፃ፣ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ድርጅት
2. ወ/ሮ ሰብለ አስቻለው አህጤኢ
19/1/2013 ዓ.ም
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *