የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ድጋፍ አደረገ፤

የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ድጋፍና እንክብካቤ ለሚያስፈልጋቸው 3 ልጆች ከ7 ሽህ ብር በላይ ግምት ያላቸው ፊኖ ዱቄት፣ መኮሮኒ፣ ፓስታ፣ የገላ ሳሙና፣ የልብስ ሳሙና፣ ዘይት እና ሳኒታይዘር ሃምሌ 23/2012 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሃተመ ሃይሌ አማካኝነት ተበርክቶላቸዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሰራተኞች ወላጆቻቸውን በሞት ያጡና እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ሶስት(03) ህፃናት ከአብክመ ጤና ቢሮ በመከበር ከደመወዛቸው በየወሩ ገንዘብ እየቆረጡ ለእያንዳንዳቸው በወር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ እየረዱ ሲሆን አሁን ካለው የኑሮ ውድነትና የኮሮና ወረርሽኝ ከመከላከል አንጻር እርዳታ አድርገዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ በርክክቡ ወቅት እንደገለፁት ልጆችን ስንቀበል ድጋፍና እንክብካቤ ማድረግ፣ መከታተል እና የተሻለ ደረጃ ለማድረስ ቃል በመግባት ሲሆን ወደፊትም ባለን አቅም ለመርዳት ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተው ልጆችም ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስን በመከላከል እና ትምህርታቸውን ጠንክረው በመማር እንዳባቸው አሳስበዋል፡፡
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *