የካይዘን ስልጠና ተሰጠ፤

ለአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በካይዘን ምንነት፣ አተገባበር እና ጠቀሜታዉ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና መስከረም 9/2013 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ ተሰጠ፡፡ የስልጠናዉ ዓላማ የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሰራተኞች በካይዘን ፍልስፍና ፅንሰ-ሃሳብ ላይ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር የካይዘን ትግበራ በተሻለና ወጥነት ባለዉ መልኩ በተቋሙ ዉስጥ እንዲተገበር፤ ህብረተሰቡ/ተገልጋዩ በአገልግሎት አሰጣጡ እንዲረካና ብክነትን ለመከላከል የአመለካከት ለዉጥ እንዲመጣ ለማስቻል ነዉ፡፡ ስልጠናዉን የሰጡት በአማራ ክልል ጤና ቢሮ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት አቶ ሞላ በላይ እንደገለፁት ካይዘን የጃፓኖች የአሰራር ፍልስፍናና በዘላቂነት ጥራትን የማረጋገጥ ስልት በመሆኑ በተቋሙ ዉስጥ ጥራት እና ለዉጥ እንዲመጣ አመራርና ሰራተኞች የካይዘን ትግበራን በስራ ቦታቸዉ በማከናወን ለለዉጥና ለጥራት በመነሳሳት ኢንስቲትዩቱ አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ ለማድረግ ንቁ ተሳታፊ መሆን አለባቸዉ ብለዋል፡፡ በስልጠናዉ የካይዘን ጥቅምና አተገባበር የቀረበ ሲሆን በተቋማት ሰራተኞችና መሪዎች መካከል የሚኖረዉን ግንኙነት በማሻሻል ንቁ ባለሙያ እንዲፈጠር ለማድረግና ደንበኞችን ለመሳብ እንዲሁም መሪዎች አዳዲስ ሃሳቦችን እንዲያመነጩ ለዉጥን እንዲደግፉና ክህሎታቸዉን እንዲያሳድጉ የሚያስችል እና በሰራተኞች ዉስጥ የባለቤትነት ስሜት እንዲጎለብትና የመፍትሄ አካል እንዲሆኑ ያስችላል ተብሏል፡፡ አህጤኢ 11/1/2013 ዓ.ም
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *