ጥራትን ያለው የላቦራቶሪ አገልግሎት ለመስጠት የውጭ ጥራት ቁጥጥር (EQA) ስራዎችን መተግበር እንደሚገባ ተገለፀ፤

የአማራ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤና ተቋማት የላቦራቶሪን የውጭ ጥራት ቁጥጥር (EQA) እና የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ማዕከላት አፈፃፀም ከህዳር 25-26/2013 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ ገምገሟል፡፡ በመድረኩ ጥራት ያለው የላቦራቶሪ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት የውጭ ጥራት ቁጥጥር (EQA) ስራዎችን መተግበር እንደሚገባል የኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ማህተመ ኃይሌ ገልፀዋል። የውጭ ጥራት ቁጥጥር (EQA) እና የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማዕከላት አፈፃፀም እንዲሁም የ2013 በጀት ዓመት የጋራ ዕቅድ ቀርቧል። የኮሮና ወረርሽኝ መከሰት፣ የግብዓት አቅርቦት እጥረት፣ የማሽን ብልሽት፣ ሪፖርት በወቅቱ አለመላክ፣ ድጋፍና ክትትል በወቅቱ አለማድረግ፣ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እና ሌሎች ችግሮችና ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ተነስተው ውይይቱ ተደርጎባቸዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ በበኩላቸው የተሰሩ ስራዎች ጥሩ መሆናቸውን ገልፀው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመሆኑ የተቀዛቀዘው የመከላከል ስራችንን መነቃቃት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም አንድ ባለሙያ ንቃተ ህሊናው ፣ ሙያውን አክብሮ የሚሰራ እና ሁለገብ መሆን እንዳለበት ገልፀው ተባብረን ከሰራን ለውጥ እናመጣለን ብለዋል፡፡ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ዶክተር ማህተመ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አውስተው የኮቪድ-19 ስራችንን ከሌሎች የጤና ስራዎች ጋር አቀናጅተው መስራት እንዲሁም የድጋፍና ክትትል ስርዓታችንን በማጠናከር የተሻለ ውጤት ለማምጣት መስራት እንዳባቸው አሳስበዋል፡፡
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *