3. የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የአብክመ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን ጉበኙ፤

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለዉ አባይነህ እና የስራ ክፍል ሃላፊዎች የአብክመ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚገኙ የላቦራቶሪ ክፍሎችን ነሐሴ 21/2013 ዓ.ም ጉብኝተዋል። በዕለቱ በሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች የአደጋ ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ዙሪያ ከተቋሙ አመሪሮችና ባለሙያዎች ጋር ዉይይት ሲሆን በሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ረገድ የተከናወኑ ተግባራትና ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ በኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ አብርሃም አምሳሉ ገለፃ ተደርጓል፡፡ የኢንስቲትዩ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ እቅድን ወደ ተግባር ከመቀየር አኳያ የክስተት አስተዳደር ስርዓቱ ላይ የተሻለ ስራ ሲሰራ መቆየቱን እና በኮቪድ-19 ምክንያት የስጋት ተግባቦትና በማህበረሰብ ተሳትፎ እንደ ሃገር ጥሩ ልምድ መገኘቱን ገልፀዉ ጦርነት ሲከሰት የስነ-ልቦና ስራ መስራት ላይ በደንብ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ ለኢንስቲትዩቱ የምናደርገዉ ድጋፍ በርቀት ብቻ መሆኑ በቂ ባለመሆኑ በአካል መገኘትና ድጋፍ ማድረጉ ወሳኝ ነዉ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ገልፀዋል፡፡ በአማራ ክልል መንግስት እና ህዝብ የተፈጠረዉን ችግር ብቻዉን ሊወጣዉ ስለማይችል ሁሉም በየደረጃዉ ያሉ አካል የሚችለዉን ሁሉ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ አስቻለዉ በጦርነቱ ለሚፈናቀሉ ዜጎች ምግብ እና መጠለያ ከማመቻቸት አልፎ የክረምት ወቅት በመሆኑ እንዲሁም በክልሉ በርካታ የፀበል ቦታዎች ያሉበትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሰባስበዉ የሚቆዩበት በመሆኑ ለኮሌራና የተለያዩ ወረርሽኞች ሊቀሰቀሱ ስለሚችሉ በጋራ ሲሰራ ይገባል ብለዋል። በተጨማሪም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁኔታ በክልሉ ያለዉን ጫና በርካታ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡ አቶ አስቻለዉ አክለዉም የዛሬዉ ጉብኝት ዓላማ ክልሉ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለማየትና የተከሰተው ችግር ለአንድ ክልል ብቻ የሚተዉ ባለመሆኑ መረጃ ከመለዋወጥ ባለፈ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እንደ ባለሙያ ቦታዉ ላይ በመቆየት መስራት ያለብንን ለመስራትና እየተጋገዝን ፈተናዉን ለማለፍ እና በ2014 በጀት ዓመት የትኞቹ ተግባራት ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል የሚለዉን ለመለየት ጭምር ነዉ ብለዋል፡፡ ለሕብረተሰብ ጤና ልማት እንትጋ! አሕጤኢ ነሐሴ 24/2013 ዓ.ም

Leave a Reply