7A (1)

ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡

በምልከታቸዉም በኢንስቲትዩቱ የሚከናወኑ ስራዎችን የጎበኙ ሲሆን ከሰራተኞችና ከተቋሙ አመራሮች ጋር ዉይይት አድርገዋል፡፡
6A (1)

በአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የልምድ ልውውጥ ተካሄደ፤

ከደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮና ከተለያዩ ተቋማት የተዉጣጡ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በክልሉ የህብረተሰብ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ለማቋቋም በአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የልምድ ልዉዉጥ አካሄዱ፡፡ የክልሉን ላቦራቶሪ ማዕከል ወደ ህብረተሰብ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ደረጃ ለማሸጋገርና ተሞክሮ ለመቀመር ባለሙያዎችና የስራ ሃላፊዎች በአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመገኘት አጠቃላይ በኢንስቲትዩቱ መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ የተከናወኑ ተግባራት፣ ጠንካራና ያጋጠሙ ችግሮች በተቋሙ የስራ ሃላፊዎችና ዳይሬክቶሬቶች ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ጎብኝዎችም በየዳይሬክቶሬቶች በመዘዋወር የስራ እንቅስቃሴዎችንም ጎብኝተዋል፡፡ አስተያየታቸዉን ከሰጡን መካከል አቶ ማሙሽ ሁሴን፣ አቶ ሙሃመድ አይኔ እና ወ/ሮ እመቤት መኮነን ለክልል ብቻ ሳይሆን ለሃገር የሚጠቅም ስራ እየተሰራ መሆኑን፣ የተቀላጠፈና የተቀናጀ የአሰራር ስርዓት የተዘረጋ መሆኑን፣ የተደራጀ የአደጋ ጊዜ ማሳለጫ ማዕከል ማቋቋም መቻሉ፣ ክልሉ ላይ የሚሰሩ ጥናቶች ወደ አንድ ቋት እየገቡና የገቢ ምንጭ እየሆኑ መሆናቸዉ በአጠቃላይ በልምድ ልዉዉጡ በቂ መረጃ እንዳገኙበትና ለሚፈልጉት ዓላማ ግብዓት ማግኘታቸዉን ገልጸዋል፡፡ አህጤኢ 09/04/2012 ዓ.ም
5A

ሳይንሳዊ ዕዉቀትን በመጠቀም የተሰሩ ጥናትና ምርምሮች ቀርበዉ የሚገመገሙበትና በአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ዳይሬክቶሬት አማካኝነት በየወሩ የሚካሄደዉ 2ኛዉ ጆርናል ክለብ /Journal Club/ ህዳር 30 ቀን 2012 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ፤

“Viral Suppression Rate Among children Tested for HIV Viral Load At The Amhara Public Health Institute” በሚል ርዕስ የተሰራ ጥናታዊ ፅሁፍ በኢንስቲትዩቱ ተባባሪ ተመራማሪ በአቶ መላሹ ባለዉ ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡ አህጤኢ 01/04/2012 ዓ.ም
2A

የአማራ ክልል የጤና ሙህራን መማክርት ጉባኤ በክልሉ የጤና ሁኔታ እና የወደፊት ስራ ላይ በባህር ዳር ከተማ ውይይት አካሄደ፡፡

በዕለቱ የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር መልካሙ አብቴ በክልሉ ያለውን የጤና ሁኔታ እና ከሙሁራኑ የሚጠበቀው በተመለከተ መነሻ ፅሁፍ ያቀርቡ ሲሆን የተለያዩ ሃሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ተሳታፊዎች የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን የጎበኙ ሲሆን ከኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማህተመ ሃይሌ እና ከባለሙያዎች ጋር ያለውን የስራ እንቅስቃሴን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል፡፡

ለአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ለመከላከልና ለመቆጣጠር ስራ እገዛ የሚያደርጉ ሞተር ሳይክሎች ድጋፍ ተደረገ፡፡

49 ሞተር ሳይክሎች ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በድጋፍ የተገኘ ሲሆን ባለፈዉ ሳምንት 38 ሞተር ሳይክሎች መግባታቸዉ የሚታወስ ነው፡፡ ቀሪ 11 ሞተር ሳይክሎች ደግሞ ወደ ተቋሙ ገብተዉ ርክክብ ተደርጓል፡፡ አህጤኢ 01/03/2012 ዓ.ም